Fana: At a Speed of Life!

የአጼ ፋሲል ቤተ መንግስትን ለማስጠገን የ400 ሚሊየን ብር ጥናት ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 15 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአጼ ፋሲል ቤተ መንግስት ህንጻዎችን ለመጠገን የ400 ሚሊየን ብር የፕሮጀክት ጥናት መጠናቀቁን የጎንደር የዓለም አቀፍ ቅርሶች አስተዳዳሪ አስታወቁ።

አስተዳዳሪው አቶ ጌታሁን ስዩም ለኢዜአ እንደገለፁት፥ የፕሮጀክት ጥናቱ በቀጣዮቹ አምስት አመታት የጥገና ስራውን ደረጃ በደረጃ ለማካሄድ የሚያስችል ነው።

በጥናቱ አማራ ክልልን ጨምሮ የፌደራል የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ከፍተኛ ባለሙያዎች ተሳታፊ መሆናቸውንም ተናግረዋል።

የጥገና በጀቱ በፌደራል መንግስት ድጋፍ እንደሚሸፈንና ዓለም አቀፍ ለጋሽ ድርጅቶችም ድጋፍ ያደርጋሉ ብለዋል።

በተያያዘም የቤተ መንግስቱ ዙሪያ አጥር ጥገና ከክልሉ መንግስት በተመደበና ከጎብኝዎች ገቢ በ36 ሚሊየን ብር መጀመሩን አስተዳዳሪው ገልጸዋል።

የፌደራል የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው የአጼ ፋሲል ቤተ መንግስት ህንጻዎችን ከተጋረጠባቸው አደጋ ለመታደግ ጥናቶች መጠናቀቃቸውን አስታውቀዋል።

በ16ኛው ክፍለ ዘመን የታነጸው የአጼ ፋሲል ቤተ መንግስት ህንፃ እንደ አውሮፓውያን የቀመር ዘመን በ1979 በዩኔስኮ በአለም የሰው ሰራሽ ቅርስነት የተመዘገበ መሆኑ ይታወቃል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.