የሀገር ውስጥ ዜና

የቀድሞው ጠ/ሚ አቶ ሃይለማርያምና ባለቤታቸው ወይዘሮ ሮማን ፋውንዴሽን መሰረቱ

By Abrham Fekede

October 16, 2020

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቀድሞው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝና ባለቤታቸው ወይዘሮ ሮማን ተስፋዬ ፋውንዴሽን መሰረቱ፡፡

ፋውንዴሽኑ “ሃይለማርያም እና ሮማን ፋውንዴሽን” በሚል ስያሜ የተመሰረተ ሲሆን ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ ሰርተፊኬት አግኝቷል፡፡