የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ ርስቱ ይርዳ የባቹማ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልን መርቀው ከፈቱ

By Tibebu Kebede

October 18, 2020

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል ምዕራብ ኦሞ ዞን የባቹማ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ተመረቀ።

ሆስፒታሉን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳ መርቀው መክፈታቸውን ከደቡብ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በዞኑ እየተከናወኑ ያሉ የመሠረተ ልማት ስራዎችን አስመልክቶ ጉብኝት አድርገዋል፡፡

ቀደም ብለው በካፋ ዞን እየለማ ያለን የስንዴ ማሳ መጎብኘታቸው ይታወሳል።

ከዚህ ባለፈም በትናንትናው እለት በዞኑ የተከናወኑ የልማት ስራዎችን መጎብኘታቸው የሚታወስ ነው።