Fana: At a Speed of Life!

ኢራን በቀጠናው የሚስተዋለውን ውጥረት መፍታት የሚያስችል የመፍትሄ ሃሳብ እንደምትቀበል ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 15፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) ኢራን በቀጠናው የሚስተዋለውን አለመግባባት መፍታት የሚያስችል ማንኛውንም የመፍትሄ ሃሳብ እንደምትቀበል አስታውወቀች።

በኢራን የውጭ ግንኙነት ስትራቴጂክ ምክር ቤት ሃላፊ ካማል ካህራዚ በኢራን የቻይና አምባሳደር ቻልግ ዩዋ ጋር በትናንትነው ዕለት ተወያተዋል።

በዚህ ወቅትም በመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት መካከል የሚስተዋለውን አለመግባባት ለመፍታት ኢራን ቁርጠኛ አቋም ያላት መሆኑን ካማል ካህራዚ ተናግረዋል።

ለቀጠናው ሰላም መደፍረስ አሜሪካና የምዕራባውን ሀገሮች ድርሻ ከፍተኛ መሆኑን ያነሱት ሃላፊው፥ችግሩንለመፍታት የአካባቢው ሀገራት በቅንጅት መስራት እንደሚገባቸው አሳስበዋል ።

ለዚህም ቴህራን የቀጠናውን ችግር ለመፍታት  ከሀገራቱ ጋር በትብብር ከመስራት ባለፈ አስፈላጊ የሆኑ የመፍትሄ ሃሳቦችን ለመቀበል ዝግጁ ነው የገለጹት።

ቻልግ ዩዋ በበኩላቸው  ቻይና ከኢራን ጋር ስትራቴጂካዊ ግንኙነት ያላት መሆኑን በመግለጽ የሀገራቱን ግንኙነት ይበልጥ ለመሳደግ በቅንጅት የሚሰራ መሆኑን አንስተዋል።

ቻይና አሜሪካ በመካከለኛው ምስራቅ የምታሳየውን እንቅስቃሴ ትቃወማለች ያሉት አምባሳደሩ ችግሩንበዘላቂነት ለመፍታት የአካባቢው ሀገራት መወያየት እንደሚገባቸው አሳስበዋል።

ምንጭ ፦https://www.presstv.com

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.