ዓለምአቀፋዊ ዜና

ጣሊያን ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ አዳዲስ እርምጃዎችን ይፋ አደረገች

By Feven Bishaw

October 19, 2020

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጣሊያን ከኮሮና ቫይረስ ጋር ተያይዞ አዳዲስ እርምጃዎችን ይፋ አደረገች፡፡

በሃገሪቱ ለተከታታይ ሁለት ቀናት ከፍተኛ ቁጥር ያለቸው ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡

ይህን ተከትሎም ሃገሪቱ ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ የተደነገጉ መመሪያዎች በማጥበቅ አዳዲስ እርምጃዎችንም ይፋ አድርጓል፡፡

በዚህም ዳግም ተከፍተው የነበሩ የምሽት መዝናኛ ቤቶች እና ምግብ ቤቶች እኩለ ሌሊት ላይ እንዲዘጉና ከዛ በኋላ ባለው ሰአት የጠረጴዛ አገልግሎት ብቻ እንዲሰጡ ተወስኗል፡፡

ከዚህ ባለፈም የሚካሄዱ ኮንፈረንሶች እና ፌስቲቫሎች እንዲታገዱ እንዲሁም ስፖርት ቤቶች እንዲዘጉም ተወስኗል ነው የተባለው፡፡

የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ጁሴፔ ኮንቴ ተጨማሪ የእንቅስቃሴ ገደቦችን ማስቀረት እንደሚፈልጉ ተናግረዋል፡፡

ይህ እንዲሆንና የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር  ደግሞ ከመንግስት ባሻገር ሁሉም የድርሻውን መወጣት አለበትም ብለዋል፡፡

አያይዘውም መሰረታዊ የጥንቃቄ እርምጃዎችን ማለትም ጭምብልን ማድረግ፣ ርቀትን መጠበቅ እና የእጅ ንፅህናን መጠበቅ፣ ከወዳጅ ዘመድ ጋር ለሚኖር ግንኙነትም ትኩረት መስጠት ይኖርብናል ነው ያሉት፡፡

ምንጭ፡-ቢቢሲ