ፋና ስብስብ

“የገና አባት” በመምሰል ባንክ የዘረፉት የ65 ዓመቱ  አዛውንት

By Tibebu Kebede

December 25, 2019

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 15፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) “የገና አባት” በመምሰል ባንክ የዘረፉት የ65 ዓመቱ አዛውንት ብዙዎቹን አስገርመዋል።

65 ዓመቱ ዴቪድ ዋይን ኮሎራዶ ወደሚገኘው የአካዴሚ ባንክ በማቅናት ነው የ “ገና አባት” በመምሰል ዘረፋውን ያከናወኑት፡፡

አዛውንቱ ባንኩን ከዘረፉ በኋላም ጎዳና ላይ በመውጣት መልካም ገና እያሉ ገንዘቡን መበተን ጀምረዋል ነው የተባለው።

በመቀጠልም አቅራቢያው ወደሚገኘው ስታርባክስ የቡና ሱቅ ተቀምጠው በቁጥጥር ስር እስኪውሉ ይጠብቁ እነደነበር ተገልጿል ፡፡

የአይን እማኞች እንደሚሉትም ባንኩን ዘርፈው ከወጡ በኋላ ገንዘቡን በአቅረቢያ ለነበሩ ሰዎች አከፋፍለዋል፡፡

ይሁን እንጂ በወቅቱ  ቦታው ላይ የነበሩ ሰዎች ገንዘቡን  ከመውሰድ ይልቅ ለተዘረፈው ባንክ መመለሳቸው ነው የተገለፀው፡፡

የኮሎራዶ ፖሊስም አዛውንቱን  በቁጥጥር ስር ያዋላቸው ሲሆን ወንጀሉን በራሳቸው ተነሳስተው የፈጸሙት መሆኑን አስታውቋል፡፡

ምንጭ፡-ቢቢሲ