የሀገር ውስጥ ዜና

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን ነገ ያካሂዳል

By Meseret Demissu

October 19, 2020

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 9 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት 8ኛ አመት 1ኛ መደበኛ ጉባኤውን ነገ ያካሂዳል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን የሚያካሂደው በፌዴሬሽን ምክር ቤት አዳራሽ መሆኑ ተገልጿል።

ነገ በሚካሄደው መደበኛ ጉባኤ የአስፈጻሚ አካላት የ2013 በጀት ዓመት የሶስት ወራት እቅድ አፈጻጸም የሚገመገም መሆኑንም የምክር ቤቱ የፕሬስና የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ አዲስዓለም እንቻለው ገልጸዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ክፍለ ከተሞችን እና ወረዳዎችን እንደገና የማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ውይይት በማካሄድ የውሳኔ ሃሳብ እንደሚያሳልፍም ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም በምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ አቅራቢነት ልዩ ልዩ ሹመቶች እንደሚሰጥም ከአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡