የሀገር ውስጥ ዜና

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የተለያዩ ሹመቶችን አፀደቀ

By Tibebu Kebede

October 20, 2020

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት በምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ አቅራቢነት ልዩ ልዩ ሹመቶችን አጸደቀ።

በዚህ መሠረት፦

1ኛ. አቶ ጥራቱ በየነ – በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የከተማ ስራ አስኪያጅ ቢሮ ኃላፊ

2ኛ. ዶክተር መስከረም ፈለቀ – ቤቶች ልማት አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ

3ኛ . ኢንጂነር አያልነሽ ሀ/ማርያም – ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ

4ኛ. ዶክተር መስከረም ምትኩ – የፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር

5ኛ. ዶክተር ሚልኬሳ  ጃጋማ – መሬት ልማት አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ

6ኛ. ዶክተር ሙሉቀን ሀብቱ – ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ

7ኛ. አቶ ተፈራ ሞላ – ሰራተኛና ማህበራዊ ቢሮ ኃላፊ

8ኛ. አቶ ሙሉጌታ ተፈራ – ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል።