Fana: At a Speed of Life!

ለሴት ተማሪዎች የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ማሰባሰቢያና ለሲ ኤን ኤን የዓመቱ ጀግና ፍሬወይኒ የአቀባበል መርሃ ግብር ሊካሄድ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 15፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ በመንግስት ትምህርት ቤት ለሚማሩ ሴት ተማሪዎች ሞዲስ እና ሌሎች የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን በነጻ ለማቅረብ የከተማ አስተዳደሩ ከተለያዩ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ ይገኛል።

በዚሁ መሰረት የፊታችን ታህሳስ 28 ቀን 2012ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ የቁሳቁስ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር መዘጋጀቱን አስተባባሪዎቹ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።

በመርሃ ግብሩ 700 ሺህ ሞዴስ እና 200 ሺሕ የሴቶች ፓንት ለማሰባሰብ እቅድ መያዙ የተገለጸ ሲሆን በመርሃ ግብሩም ከ20 ሺህ በላይ በጎ ፍቃደኞች ተሳታፊ ይሆናሉ ተብሏል።

በዚህ ዕለትም በአሜሪካው የዜና አውታር ሲ.ኤን.ኤን የአመቱ ጀግና ተብላ የተሸለመቺው ፍሬወይኒ መብረሃቶም የክብር አቀባበል እንደሚደረግላት ተገልጿል።

ማንኛውን የከተማዋ ነዋሪዎች መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት የሚችሉትን ሞዴስ ፣የሴቶች ፓንት እና ሌሎች የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን በመያዝ መግባት እንደሚችሉ አዘጋጆቹ አመልክተዋል።

ማንኛዉም ሰዎች የሚሉችን ሞዴስ እና የሴቶች ፓንት እንደመግቢያ መያዝ በፕሮግራሙ መታደም እንደሚችሉ ከከተማው ፕሬስ ሴክሬተሪያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ በትምህርት ላይ ከሚገኙ ጠቅላላ ተማሪዎች ከ50 በመቶ በላዩ ሴቶች ሲሆኑ በየወሩ ከሁለት እስከ ሶስት ቀናት ከወር አበባ ጋር ተያያዥ በሆኑ ጉዳዮች ከትምህርት ቤት እንደሚቀሩ ጥናት ማመልከቱ ተጠቁሟል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.