የሀገር ውስጥ ዜና

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ ከኢ/ር ታከለ ጋር አዲስ አበባ በዲፕሎማሲው ዘርፍ ባለት ሚና ላይ ያተኮረ ውይይት አካሄዱ

By Tibebu Kebede

December 25, 2019

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 15፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ጋር ተወያይተዋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ እና ምክትል ከንቲባው አዲስ አበባ ከተማ በዲፕሎማሲው ዘርፍ ባለት ሚና ላይ ያተኮረ ውይይት ማድረጋቸውን ምክትል ከንቲባው በፌስቡክ ገፃቸው አስፍረዋል፡፡