ስፓርት

በወዳጅነት ጨዋታ ዋልያዎቹ በዛምቢያ አቻቸው ተረቱ

By Tibebu Kebede

October 22, 2020

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ዋልያዎቹ) ከዛምቢያ አቻው ጋር የወዳጅነት ጨዋታ አካሂደዋል።

በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ኢትዮጵያ እስከ 86ኛው ደቂቃ ድረስ 2-1 ስትመራ ብትቆይም፤ ተቀይሮ የገባው አልበርት ካዋንዳ አከታትሎ ባስቆጠራቸው ጎሎች የዛምቢያ ብሄራዊ ቡድን 2ለ3 በሆነ ውጤት ጨዋታውን አሸንፎ ወጥቷል።