Fana: At a Speed of Life!

ዳሽን ባንክ በ100 ሚሊየን ብር የስራ እድል ፈጠራ ፕሮጀክት ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 16 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ዳሽን ባንክ በ100 ሚሊየን ብር የስራ እድል ፈጠራ ፕሮጀክት ይፋ አደረገ።

የኢትዮጵያ ታለንት ፓወር ሲሪየስ የሚል መጠሪያ የተሰጠው ይህ ፕሮጀክት፥ ስራ ፈጠራን ማበረታታት፣ ክህሎት ላላቸው ዜጎች የገንዘብ ድጋፍ ማድረግና የስራ አጥነትን ለመቅረፍ ያግዛል ነው የተባለው።

ከዚህ ባለፈም ለሃገራዊው የኢኮኖሚ ማሻሻያ እቅድ ትግበራ የራሱን ሚና ይወጣል ተብሎም ይጠበቃል።

ፕሮጀክቱ በዚህ አመት በተመረጡ ስድስት ከተሞች ተግባራዊ እንደሚደረግም ባንኩ አስታውቋል።

በፕሮጀክቱ ተጠቃሚ የሚሆኑ ዜጎችም የስራ ፈጠራ ክህሎትና የአቅም ግንባታ ስልጠና የሚያገኙ ሲሆን፥ ስራ መጀመር የሚያስችል ድጋፍም ከባንኩ ያገኛሉ።

ፕሮጀክቱ የስራ ፈጠራ ስልጠና፣ የጥቃቅን እና አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች አቅም ግንባታ፣ የከፍተኛ ትምህርት የፋይናንስ ድጋፍ መርሃ ግብር፣ የፋይናንስ ተደራሽነት መርሃ ግብር፣ የቢዝነስ ክለብ ምስረታ፣ የገበያ ትስስር እና የእሴት ሰንሰለት የፋይናንስ ድጋፍ ላይ ትኩረቱን ያደርጋል።

በአወል አበራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.