የሀገር ውስጥ ዜና

629 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ19 ሰዎች ህይወት አልፏል

By Meseret Demissu

October 24, 2020

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 7 ሺህ 454 የላቦራቶሪ ምርመራ 629 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል ።

በዚህም በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 92 ሺህ 858 ደርሷል።