Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቅጥር ለመፈፀም ሁለት ቋንቋን መቻል የሚያስገድድ ህግ አልወጣም – አቶ ዣንጥራር አባይ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 15፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሁለት ቋንቋዎችን እንደግዴታ ያስቀመጠበት ህግ እንዳላወጣ አስታወቀ፡፡

ቅጥርን በተመለከተ ከተማ አስተዳደሩ ሁለት ቋንቋዎችን እንደግዴታ አስቀምጧል እየተባለ የተናፈሱ መረጃዎች ከእውነት የራቁ መሆናቸውን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ዣንጥራር አባይ ገለጹ፡፡

አቶ ዣንጥራር በጉዳዩ ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

አቶ ዣንጥራር ከተማ አስተዳደሩ በቻርተር የሚተዳደር እና ቻርተሩን በ1995 በአዋጅ የቻርተር አዋጅ 361 ተብሎ በግልጽ እንደተቀመጠው አማርኛ የከተማ አስተዳደሩ የስራ ቋንቋ ሆኖ እንደሚያገለግል በግልጽ መቀመጡን አስታውሰዋል፡፡

ይህ ቻርተር የወጣው በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አማካኝነት ስለሆነ አዋጁ ባልተሻሻለበት ሁኔታ ስራ ለመቀጠር ሁለት ቋንቋ እንደግዴታ ነው እየተባለ የሚነዛው ወሬ ከእውነት የራቀ ነው ብለዋል፡፡

ከተማ አስተዳደሩ ስራ ለመቀጠር እንደግዴታ ያወጣው ህግ ባለመኖሩ ምናልባት በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ሁለት ቋንቋ መቻልን እንደግዴታ የሚያስቀምጡ ማስታወቂያዎችን ካሉ ትክክል ባለመሆኑ ከተማ አስተዳደሩ እርምጃ እንደሚወስድ ገልጸዋል፡፡

በፍሬህይወት ሰፊው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.