ስፓርት

ሀዋሳ ከተማ ኤፍሬም አሻሞን አስፈረመ

By Tibebu Kebede

October 26, 2020

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 16 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የመስመር አጥቂው ኤፍሬም አሻሞ ከመቐለ 70 እንደርታ ወደ ሀዋሳ ከተማ በአንድ አመት ውል ተዘዋውሯል፡፡

በቀድሞ ተጫዋቹ ሙሉጌታ ምህረት የሚሰለጥነው ሃዋሳ ከኤፍሬም አሻሞ በተጨማሪም ከደቡብ ፖሊስ ተከላካዩ ዘነበ ከድር እና ግብ ጠባቂውን ዳግም ተፈራ (ቻቺ) በአዲስ ውል ፈርመው ውላቸው ፀድቋል፡፡

በተመመሳሳይ ክለቡ ሰሞኑን የበርካታ ተጨዋቾችን ውል ያራዘመ እና አዲስ ተጨዋቾች ማስፈረሙን ከኢትዮ ኪክ ኦፍ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።