የሀገር ውስጥ ዜና

ሁለት የውጭ የቴሌኮም ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ስራቸውን እንዲከውኑ ፍቃድ እንደሚሰጣቸው ተገለጸ

By Meseret Demissu

October 27, 2020

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 17 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)ሁለት የውጭ የቴሌኮም ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ስራቸውን እንዲከውኑ ፍቃድ እንደሚሰጣቸው ተገለጸ፡፡

በትናንትናው ዕለት የቴሌኮም ዘርፍ የማሻሻያ ስራዎች ሂደት ላይ ያተኮረ ውይይት በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ተካሄዷል፡፡

አዳዲስ የቴሌኮም ኦፕሬተሮችን ወደሃገር ውስጥ በማስገባት ዘርፉን ለውድድር ክፍት ለማድረግ እና የኢትዮ ቴሌኮምን ድርሻ በከፊል ለማዛወር እስካሁን የተሰሩ ስራዎች በውይይቱ ሪፖርት ቀርቧል፡፡

በዚህም የውጭ የቴሌኮም ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ስራቸውን እንዲከውኑ ፍቃድ እንዲሰጣቸው ውሳኔ ማሳለፈቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በፌስ ቡክ ገጻቸው ላይ ገልጸዋል፡፡

አያይዘውም ኢትዮ ቴሌኮምን በከፊል ወደ ግል ይዞታ የማዛወር ሥራ የኢትዮጵያ ጥቅም ባስጠበቀ መልኩ እንደሚቀጥል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡