Fana: At a Speed of Life!

አዲስ እየተዘጋጀ ባለው የማዕድንና ነዳጅ ረቂቅ ፖሊሲ ላይ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ እየተዘጋጀ ባለው የማዕድንና ነዳጅ ረቂቅ ፖሊሲ ላይ ውይይት ተካሂዷል።
 
በውይይቱ ላይ የማዕድን ነዳጅ ሚኒስትር ኢንጅነር ታከለ ኡማና የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴን ጨምሮ የማይክሮ ኢኮኖሚ አማካሪ ቡድን አባላትና በዘርፉ ረጅም አመት ልምድ ያላቸው ሀላፊዎችና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።
 
በማዕድንና ነዳጅ ዘርፍ እስካሁን ፖሊሲ ያልነበረ ሲሆን ዘርፉ በአዋጅና መመሪያዎች የሚመራ ነበር ተብሏል።
 
ከውይይቱ የተገኙ ግብአቶች ተጨምረውበት ረቂቅ ፖሊሲው ለሚኒስትሮች ምክር ቤት እንደሚላክ ተጠቁሟል።
 
ፖሊሲው ኢትዮጵያ ከአስር ዓመት በኋላ ጋዝ ለማምረት የሚያስችላት መሆኑን ነው የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ያስታወቀው፡፡
 
ይህም ሃገሪቱ በሚገባ ሳትጠቀምበት የቆየችውን የተፈጥሮ ሃብት አቅሟ ለገበያ በማቅረብ የውጭ ምንዛሪ እንድታገኝበት የሚያደርግ በመሆኑ ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር ማደረግ እንደሚገባ በምክክር መድረኩ ተመላክቷል፡፡
 
ፖሊሲው ዘርፉን በማዘመን ሌላኛው የሃሪቱ የዕድገት አቅጣጫ ትኩረት ለማድረግ ያቀደ መሆኑ ተገልጿል፡፡
 
በፖሊሲ ምክክሩ ከአምስት አመት በኋላ የመጀመሪያው የነዳጅ ምርት ይገኛል በሚል ረቂቅ ፖሊሲው ያቀረበው ምክረ ሃሳብ ላይ አስተያየት ተሰጥቶበታል፡፡
 
በሶዶ ለማ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.