የሀገር ውስጥ ዜና

በጉራ ፈርዳ ወረዳ ለሰው ህይወት መጥፋት እና ለንብረት ውድመት ምክንያት ናቸው ተብለው የተጠረጠሩ 54 ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

By Feven Bishaw

October 27, 2020

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በቤንች ሸኮ ዞን ጉራ ፈርዳ ወረዳ ለሰው ህይወት መጥፋት እና ለንብረት ውድመት ምክንያት ናቸው ተብለው የተጠረጠሩ 54 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ፡፡

የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ፍቅሬ አማን እንደገለጹት ሰሞኑን በጉራ ፈርዳ ወረዳ ለ31 ሰዎች ሞት ለንብረት ውድመት እና ለአካል ጉዳት መንስኤ ናቸው ተብለው የተጠረጠሩ 54 ሰዎች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡