ቢዝነስ

ከ30 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ

By Meseret Demissu

October 27, 2020

አዲስ አበባ ፣ጥቅምት 17 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)ከ30 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የኮንትሮባንድ ዕቃ መያዙ ተገለጸ።

የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ÷ በአምስት የተለያዩ መጋዘኞች ውስጥ ተከማችተው የተገኙ 30 ሚሊየን 174 ሺህ 255 ብር ግምት ያላቸው የተለያዩ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በህብረተሰቡ ጥቆማ መያዛቸውን አስታውቀዋል።