Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ የውጭ እና የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች የሶስትዮሽ ስብሰባ መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ የውጭ እና የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች በህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ስብሰባ መካሄድ ጀመረ።

በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ የሚካሄደው የሶስትዮሽ ስብሰባ ዛሬ ጥቅምት 17 ቀን 2013 ዓ.ም በኢንተርኔት አማካኝነት በቨርቹዋል መካሄድ መጀመሩን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።

የዛሬው ስብሰባ ሊጀመር የቻለው በደቡብ አፍሪካ የዓለምአቀፍ ግንኙነትና ትብብር ሚኒስትር እና የአፍሪካ ህብረት አስፈጻሚ ምክር ቤት ሊቀመንበር ጥቅምት 11 ቀን 2013 ዓ.ም ለሀገራቱ በጻፉት ደብዳቤ ባስተላለፉት ጥሪ መሰረት ነው።

በዚህ መሰረት የኢትዮጵያ፣ ግብፅ እና ሱዳን የውጭ ጉዳይ እና የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች የቨርቷል ስብሰባ ከቀኑ 10 ስዓት ላይ ተጀምሮ እየተካሄደ ይገኛል።

ስብሰባው በአፍሪካ ህብረት ማዕቀፍ ስር እየተካሄደ ያለው የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን የተመለከተው የሶስትዮሽ ድርድር በሚቀጥልበት ጉዳይ ዙሪያ የሚመክር ይሆናል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.