Fana: At a Speed of Life!

ዩ.ኤስ.ኤይድ ኢትዮጵያ የጀመረችውን የሴቶችን ጫና የሚያቃልሉ ቴክኖሎጂዎች ዝርጋታን በገንዘብ እደግፋለሁ አለ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 16፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (ዩ.ኤስ.ኤይድ)ኢትዮጵያ የጀመረችውን የሴቶችን ጫና የሚያቃልሉ ቴክኖሎጂዎች ዝርጋታን በገንዘብ እንደሚደግፍ አስታወቀ።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ጀማል በከር የድርጅቱ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ሲያን ጆንስን ጋር በዛሬው እለት ተወያይተዋል።

በዚሁ ወቅትም የዩ.ኤስ.ኤይድ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ሲያን ጆንስን፥ ኢትዮጵያ የጀመረችውን ምቹ የኢኖቬሽን ከባቢያዊ ሁኔታ መደገፍ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል።

በኢትዮጵያ ምቹ የኢኖቬሽን ከባቢያዊ ሁኔታ ለመፍጠር የሚደረገውን ጥረት፣ ግብርናን በቴክኖሎጂ ለማዘመን፣ ታዳሽ ሃይልን ለማህበረሰቡ ለማዳረስ፣ የቴክኖሎጂ ማበልፀጊያ ማዕከል ለማቋቋም የሚደረገውን ጥረት እንደሚደግፍም አስታውቀዋል።

በተለይ የሴቶችን ጫና በሚያቃልሉ ቴክኖሎጂዎች ዝርጋታ ላይ የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን የድርጅቱ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ሲያን ጆንስ ተናግረዋል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ጀማ በከር ሴቶች ስራ እና ሃብት በመፍጠር በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ውስጥ የራሳቸውን ድርሻ እንዲጫወቱ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

ለዚህ ስኬትም የዩ ኤስ ኤይድ ድጋፍ አስተዋፅኦው የጎላ መሆኑን ማብራራታቸውንም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.