Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ከ18 ቀናት በኋላ በሕንድ ውቅያኖስ ውስጥ በህይወት የተገኙት ዓሳ አጥማጆች

KENYA - MARCH 18: Boats in the Indian Ocean near Mombasa, Kenya. (Photo by DeAgostini/Getty Images)

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 16፣2012(ኤፍ.ቢ.ሲ) 8 የኬንያ ዓሣ አጥማጆች ከ18 ቀናት በኋላ በሕንድ ውቅያኖስ ውስጥ በህይወት መገኘታቸው ተሰምቷል

ፖሊስ በሕንድ ውቅያኖስ  ከ18 ቀናት ቆይታ በኋላ በተዓምር  በሕይወት የተረፉ ስምንት ዓሳ አጥማጆች ማግኘቱን አስታውቋል።

ስምንቱ ኬንያውያን በባህር ኃይል ፖሊሶች  ነው  በገና በዓል ዕለት የተገኙት።

የማሊንዲ  አውራጃ ፖሊስ አዛዥ ቪታኒስ ኦቲኖ  ጀልባዋ ወደ ጥልቁ ውሃ የሰጠመችው በኃይለኛ  የነፋስ ሞገድ  ምክንያት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ዓሳ አጥማጆቹ በሰሜናዊ ጠረፍ በሚገኘው ዚዋዩ የባህር ዳርቻ ላይ እንደጠፉ እና የአልሃፊዳህ ፋይበር 15ኤች.ፒ ጀልባ እየተጠቀሙ እንደነበሩ ተነግሯል ፡፡

ስምንቱ በሕይወት ከተገኙ በኋላ ለህክምና ምርመራ ወደ ማሊዲን አውራጃ  ሆስፒታል መወሰዳቸው ታውቋል፡፡

ሰዎቹ በትክክል መቼ እንደጠፉ ሪፖርት አለመደረጉን የገለጸው ፖሊስ  ታህሳስ 8 ወደ ተለመደ ተግባራቸው ዓሳ ለማጥመድ  እንደወጡ አለመመለሳቸውን  ዘመዶችና ጓደኞቻቸው  መናገራቸውን አስታውቋል

የኬንያ የባህር ዳርቻ  የሚኖሩ  አብዣኞቹ ሰዎች ኑሯቸው  በአሳ ማጥመድ  እና በቱሪዝም ላይ የተመሰረተ በመሆኑ መሰል አደጋዎችን ማስተናገድ የተለመደ ነው።

ምንጭ፡-ሲ.ጂ.ቲ.ኤን

 

Exit mobile version