Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ የድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርክን እና የእንስሳት ስጋ ምርትን ለውጭ ገበያ ለማቅረብ የሚያስችል ቄራን መረቁ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርክን እና የእንስሳት ስጋ ምርትን ለውጭ ገበያ ለማቅረብ የሚያስችል ቄራን መርቀው ከፍተዋል።
 
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ መርቀው የከፈቱት የድሬዳዋ ኢንዱስትሩ ፓርክ በ150 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው ነው ተብሏል።
 
የኢንዱስትሪ ፓርኩ ለ1 ሺህ ዜጎች የስራ እድል መፍጠሩ ተገልጿል።
 
ፓርኩ በሙሉ አቅሙ ስራ ሲጀምር 20 ሺህ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል እንደሚፈጥር ይጠበቃል ነው የተባለው።
 
የኢንዱስትሪ ፓርኩ 15 ሼዶች ሲኖሩት÷ በአልባሳት እና ጨርቃጨርቅ ምርት ላይ የተሠማሩ አራት ኩባንያዎች ሥራ መጀመራቸውም ተገልጿል።
 
የኢንዱስትሪ ፓርኩ በ150 ሚሊየን ዶላር ወጪ የተገነባ ነው ሲል ኢዜአ ዘግቧል ።
 
በተመሳሳይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከድሬድዋ 5 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የተገነባውን የእንስሳት ስጋ ምርትን ለውጭ ገበያ ለማቅረብ የሚያስችል ቄራ መርቀዋል።
 
ይህ ቄራ በቀን ከ100 በላይ ግመል እና ከ3ሺህ በላይ በግ እና ፍየል በማረድ አቀነባብሮ ለውጭ ገበያ ለማቅረብ የሚያስችል አቅም ያለው ነው ተብሏል።
 
ይህም በአካባቢው ያለውን ሰፊ የቁም እንስሳት ሀብት በመጠቀም የውጭ ምንዛሬ ለማግኘት የሚያስችል ከመሆኑም ባለፈ ለአካባቢው ማህበረሰብ የስራ እድል ለመፍጠር የሚያግዝ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል።
 
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.