Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ በኦሮሚያ ጎሮ ጉቱ ወረዳ የአንበጣ መንጋ ያደረሰውን ጉዳት ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኦሮሚያ ጎሮ ጉቱ ወረዳ የአንበጣ መንጋ ያደረሰውን ጉዳት ጎብኝተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሶማሌ ክልል እና በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ሲያደርጉ የነበረውን የልማት ፕሮጀክት ጉብኝቶችን በማገባደድ ነው በኦሮምያ ምስራቅ ሀረርጌ ዞን በጎሮ ጉቱ ወረዳ የአንበጣ መንጋ ያደረሰውን ጉዳት የጎበኙት።

ዶክተር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ÷ መንግስት ባከናወነው የመከላከል ስራ የከፋ ጉዳት እንዳይደርስ ማስቆም ተችሏል ብለዋል።

በአንበጣ መንጋው ጉዳት ለደረስባቸው የአካባቢው አርሷደሮችንም ተገቢው ድጋፍ እንደሚደረግም ገልጸዋል።

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.