የሀገር ውስጥ ዜና

ጠ/ሚ ዐቢይ ከፌደራል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እና ከክልል ርዕሰ መስተዳድሮች ጋር ተወያዩ

By Tibebu Kebede

October 30, 2020

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከፌደራል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እና ከክልል ርዕሰ መስተዳድሮች ጋር ተወያዩ፡፡

ውይይቱ በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ እንደነበር ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስ ቡክ ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ አስታውቀዋል፡፡

በዚህም በሃገሪቱ የጸጥታ ጉዳይና ባጋጠሙ ሰው ሠራሽና የተፈጥሮ አደጋዎች ላይ ትኩረት አድርገው መክረዋል፡፡