የሀገር ውስጥ ዜና

ነገ የእስልምና እምነት ተከታዮች ሰልፍ እንዲያካሂዱ የተጠራው ሰልፍ እውቅና የለውም-የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት

By Tibebu Kebede

December 26, 2019

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 16፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ነገ የእስልምና እምነት ተከታዮች ሰልፍ እንዲያካሂዱ የተጠራው ሰልፍ ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት እውቅና ውጪ መሆኑ ተገልጿል።

የምክር ቤቱ ጸሀፊ ሀጂ ሼህ ቃሲም ታጁዲን ጉዳዩን አስመልክተው ዛሬ ማምሻውን በሰጡት መግለጫ፥ ሰሞኑን በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን ሞጣ ከተማ የተከሰተውን አደጋ ተከትሎ ተጠራ የተባለው ሰልፍ ከምክር ቤቱ እውቅና ውጪ መሆኑን አስታውቀዋል።