ስፓርት

ተመስገን ዳና የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ በመሆን ተሾሙ

By Abrham Fekede

October 30, 2020

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አሰልጣኝ ተመስገን ዳና የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ወንዶች ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ በመሆን ተሾሙ።

አሰልጣኝ ተመስገን ዳና የአንድ ዓመት ውል ኮንትራት ቀርቦላቸው ፊርማቸውን አኑረዋል፡፡

አሰልጣኙ በሴካፋ ተፎካካሪ እና ውጤታማ ቡድን እንዲሰሩ ግዴታ እንደተጣለባቸው ከፌዴሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከዚህ ቀደም ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በመያዝ በሴካፋ የፍጻሜ ተፋላሚ ማድረጋቸው የሚታወስ ነው።