ቢዝነስ

የላልይበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ከነገ ጀምሮ ለጎብኚዎች ክፍት ይሆናሉ

By Tibebu Kebede

October 31, 2020

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የላልይበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ከነገ ጀምሮ ለጎብኚዎች ክፍት እንደሚሆኑ ቱሪዝም ኢትዮጵያ አስታወቀ።

የቱሪዝም ኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር አቶ ስለሺ ግርማ ለኢዜአ እንዳሉት የላልይበላ ውቅር አብያተክርስቲያናት ከነገ ጀምሮ ለጎብኚዎች ክፍት ይሆናሉ፡፡

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወደ ኢትዮጵያ ከገባ በኋላ የወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተከትሎ በሃገሪቱ የሚገኙ የቱሪዝም መዳረሻዎች ለጎብኚዎች ዝግ ሆነው መቆየታቸው ይታወሳል።

ቱሪዝም ኢትዮጵያ በአማራ ክልል ላልይበላ ከተማ በቱሪዝም ዘርፍ ለተሰማሩ ባለድርሻ አካላት በጎብኚዎች ደህንነት አጠባበቅ፣ ለጎብኚዎች መረጃ አሰጣጥ እና በሃገር አቀፍ የቱሪዝም መለያ ዙሪያ ስልጠና ሰጥቷል።

ስልጠናው ከጎንደር፣ ባህርዳር፣ ላልይበላ እና ደባርቅ አካባቢ ለተውጣጡ ከ600 በላይ ለሆኑ አስጎብኚዎች፣ የሆቴል ባለቤት ተወካዮች፣ ድጋፍ ሰጪዎች እና የደህንነት ጠባቂ ባለሙያዎች የተሰጠ ነው።