ዓለምአቀፋዊ ዜና

በአሜሪካ ባለፉት 24 ሰዓታት 94 ሺህ ሰዎች ኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል

By Tibebu Kebede

October 31, 2020

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ ባለፉት 24 ሰዓታት ብቻ 94 ሺህ ሰዎች ኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡

ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥርም ከሰሞኑ ከተመዘገቡት ከፍተኛው ነው ተብሏል፡፡

ባለፈው ሃሙስም 91 ሺህ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የተነገረ ሲሆን ከዚያን ጊዜ ወዲህም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል ነው የተባለው፡፡

እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 9 ሚሊየን መድረሱንም የጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ ያመላክታል፡፡

አንዳንድ ግዛቶችም ከፕሬዚዳንታዊ ምርጫው ጋር ተያይዞ ለምርጫና ለድጋፍ ለሚወጡ ዜጎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል በመስጠት የሙቀት መጠናቸውን ሲለኩ ነበር፡፡

በአንዳንድ አካባቢዎችም ከቫይረሱ ስጋት ጋር ተያይዞ ትላልቅ ዝግጅቶች ከአዳራሽ ውጭ እየተደረጉ ነው።

ምንጭ፦ ቢቢሲ