የኦሮሞና የአማራ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ የምክክር መድረክ በባህርዳር ይካሄዳል
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 21፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የኦሮሞና የአማራ የፖለቲካ ፓርቲዎች በአዳማ ከተማ ያካሄዱት የጋራ የምክክር መድረክ ተጠናቀቀ።
በመድረኩ በኦሮሚያ እና በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተሳታፊዎች የጋራ ምክክር መድረክ በአራት ነጥቦች ስምምነት ላይ በመድረስ ነው የተጠናቀቀው።
በዚህም በኢትዮጵያ ከቅርብ አመታት ወዲህ እየታየ ባለው ፈጣን ሀገራዊ የለውጥ ሂደት እያመጣቸው የሚገኙ መልካም አጋጣሚዎችን በመጠቀም በተለያዩ ባለድርሻ አካላት መካከል ሁሉን አቀፍ ፓለቲካዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር እየተከናወኑ መገኘታቸው እና በዜጎች መካከል ተደማምጦ የመወያየት እና የመመካከር ባህል በማጎልበቱ ረገድ እንዲሁም የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታን በማሳደጉ ረገድ ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ተጠቁሟል።
በመሆኑ እነዚን ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸውን የምክክር መድረኮች እንዲሰፉ ከማድረግ አንፃር መንግስትን ጨምሮ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ተገቢ የሆኑ የተግባር እርምጃዎችን እንዲወስዱ የጋራ የምክክር መድረክ ጥሪ አቅርቧል።
ከዚህ በኋላ የሚደረጉ ቀጣይ መድረኮች ሁሉንም ወገኖች ባካታተተ መልኩ እንዲከናወኑ ጥሪ ያቀረበው የምክከር መድረኩ በቀጣይ በባህርዳር በሚካሄደው የምክክር መድረክ አሁን በተካሄደው መድረክ የተገኙ መልካም በማጎልበት እና ተግዳሮቶችን አማልቶ እንዲከናወን ሙሉ ድጋፋቸውን እንደሚሰጡ ተሳታፊዎቹ አስታውቋል።
ሀገራዊ ዲሞክራሲ ስርአት ግንባታን በተጨባጭ እውን ለማድረግ መላው ሀገሪቱ ዜጎች ትርጉም ያለው ተሳትፎ በማድረግ በተጨባጭ ከሚገኙ ውጤቶች ተቋዳሽ እንዲሆኑም ጥሪ አቅርቧል።
በሀገሪቱ ተጨባጭ ሁኔታ እየታዩ የሚገኙ የጥላቻ እና ግጭት ክፍተቶች ሀገሪቱን አስጊ ሁኔታ ላይ እደጣላት ግንዛቤ መያዙን ያስታወቀው መድረኩ በዋናነት መነሻዎቻቸው በህዝቦች መካከል የሚደረጉ ሳይሆኑ በተወሰኑ አካላት የሚመነጩ ከመሆናቸው የተነሳ በመድረኩ የታደሙ ባለድርሻዎች ህዝቡ በተቻለው መጠን ህብረቱን ጠብቆና አስተሳስሮ የሚገጓዝበን አስተምህሮዊ ተግባቦት ለመፍጠር ስምምነት ላይ መድረሳቸውም ነው የተነገረው።
በፀጋዬ ንጉስ እና ታሪክ አዱኛ