Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ እና ሌተናል ጄኔራል አብዱልፈታህ አል ቡርሃን የአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የሱዳን ሉአላዊ ምክር ቤት ሰብሳቢ ሌተናል ጄኔራል አብዱልፈታህ አል ቡርሃን የአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክን ጎበኙ፡፡
ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ አዲስ አበባ የገቡት የሱዳን ሉአላዊ ምክር ቤት ሰብሳቢ ሌተናል ጄኔራል አብዱልፈታህ አል ቡርሃን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር በመሆን የአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክን ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝቱ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ ሌሎች የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል ተገኝተዋል፡፡

ሌተናል ጄኔራል አብዱልፈታህ አል ቡርሃን በኢትዮጵያ በሚኖራቸው የሁለት ቀናት ቆይታ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር በሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

 

በዓላዛር ታደለ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.