የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አመራሮች የጥፋት ኃይሎች ባደረሱት ጥቃት የተሰማቸውን ሐዘን ገለጹ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አመራሮች በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ወለጋ ዞን ጉሊሶ ወረዳ ጋዋ ቀናቲ ቀበሌ የጥፋት ኃይሎች ባደረሱት ጥቃት የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን ገለጹ፡፡
አመራሮቹ ድርጊቱን በማውገዝ ፀረ-ሰላም ኃይሎች በአፋጣኝ ተይዘው ለህግ እንዲቀርቡ ለማድረግ የበኩላቸውን እንደሚወጡም ገልጸዋል፡፡
በሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚፈፀሙ እንዲህ ዓይነት እኩይ ተግባራትን አምርረው በፅናትና በቁርጠኝነት እንደሚታገሉም ነው ያስታወቁት።
አመራሮቹ ለቤተሰቦቻቸው እና ወዳጅ ዘመዶቻቸው እንዲሁም ለመላው ኢትዮጵያውያን መጽናናት መመኘታቸውን ከከተማው አስተዳደር ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።