Fana: At a Speed of Life!

የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር ሌተናል ጄኔራል አብዱልፈታህ አል ቡርሃን የኢትዮጵያ ጉብኝታቸውን አጠናቀቁ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር ሌተናል ጄኔራል አብዱልፈታህ አል ቡርሃን በኢትዮጵያ ለሁለት ቀናት ያደረጉትን ጉብኝት አጠናቀቁ።
 
ባለፈው እሁድ አዲስ አበባ የገቡት ሊቀመንበሩ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ዛሬ ጠዋት ካርቱም ተመልሰዋል።
 
ሌተናል ጄኔራል አብዱልፈታህ አል ቡርሃን በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው የኢንዱስትሪ ፓርኮችን፣ የግብር እና የኢንቨስትመንት ስራዎችን ጎብኝተዋል።
 
በዚህም ጉብኝታቸው የሰን ሽንግ ፋርማሲዩቲካል ፋብሪካ የሚያመርታቸውን የህክምና መድሀኒቶች እና የኦክስጅን የምርት ሂደት ተመልክተዋል።
 
እንዲሁም በኢስተርን ኢንዱስትሪ ዞንና ቢሾፍቱ አቅራቢያ የሚገኝ ጆይ ቲክ የተባለ ዘመናዊ የግብርና ማዕከልንም ጎብኝተዋል።
 
ሊቀመንበሩ በቆይታቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር በሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ዙሪያም መክረዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.