Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂ ማህማት በሰላማዊ ዜጎች ላይ የተፈፀመውን ጥቃት አወገዙ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂ በሰላማዊ ዜጎች ላይ የተፈፀመውን ጥቃት አወገዙ።
 
በምዕራብ ወለጋ ጉሊሶ ወረዳ በተፈጸመ ጥቃት ንጹሃን ዜጎች መደላቸው ይታወሳል፡፡
ሊቀ መንበሩም ጥቃቱን በማውገዝ በጥቃቱ ህይወታቸውን ላጡ ቤተሰቦች መፅናትን ተጎጂዎች ደግሞ በፍጥነት እንደሚያገግሙ መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።
 
የኮሚሽኑ ሊቀመንበር መንግስት በሰላማዊ ዜጎች ላይ ጥቃት የፈፀሙ አካላትን በቁጥጥር ስር በማዋል ተጠያቂ እንዲያደርግም ጠይቀዋል።
 
እየጨመረ የመጣውን ጥቃት ለመቀነስ ሁሉም አካላት ከፀብ አጫሪ ድርጊቶች በመታቀብ ውጥረቶችን ለመቀነስ እንዲሰሩም አጽንኦት ሰጥተዋል።
በሃገሪቱ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ተዋናዮችም አካታችና ሁሉን አቀፍ ውይይት በማድረግ በቁልፍ ጉዳዮች ላይ ብሄራዊ መግባባት ላይ እንዲደርሱም ነው ያሳሰቡት።
 
ሊቀመንበሩ የአፍሪካ ህብረት የኢትዮጵያ መንግስት እያካሄዳቸው የሚገኙ ለውጦችን እንደሚደግፍ በመግለፅ ሰላም እና ደህነነትን ለማረጋገጥ ህብረቱ ከኢትዮጵያ ጎን መሆኑን ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.