የሀገር ውስጥ ዜና

ህወሓት የከፈተውን ጦርነት ለመቀልበስና ቡድኑን ለማጥራት ከመንግስትና ከህዝብ ጋር እንሰራለን – አቶ ሽመልስ አብዲሳ

By Tibebu Kebede

November 04, 2020

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ህወሓት የከፈተውን ጦርነት ለመቀልበስና ቡድኑን ለማጥራት ከመንግስትና ከህዝብ ጋር እንሰራለን አሉ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ፡፡

የህወሓት የጥፋት ቡድን ተስፋ በመቁረጥ የሀገር መከላከያ ካምፕን በማጥቃቱ እርምጃ እየተወሰደ ነው አሉ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ፡፡

ቡድኑ በሀገራችን የተለያዩ አካባቢዎች የታጠቁ ኃይሎችን በመሳሪያና በገንዘብ በመደገፍ ሰላም ሲያናጋ ቆይቷል ብለዋል፡፡

ህወሓት ሌሊት ላይ የሀገር ሉዓላዊነትን በሚጠብቅ የመከላከያ ካምፕ ላይ ጥቃት በመክፈት ጦርነት መጀመሩን አቶ ሽመልስ በሰጡት መግለጫ አንስተዋል፡፡

ይህ ህገወጥ ቡድን ኦነግ ሸኔን በማስታጠቅና በመርዳት የጥፋት ስራ ሲሰራ ቆይቷልም ብለዋል፡፡

ቡድኑ አሁን ተስፋ መቁረጥ ውስጥ በመግባት የመጨረሻ የጣረሞት እየተፍጨረጨረ ይገኛል ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፡፡

ሲያሰለጥናቸው በቆየው ኃይልም በሰላማዊ ዜጎች ላይ ጥፋት ሲፈፅምና ሲያስፈፅም ቆይቷል ነው ያሉት፡፡

ህወሓት የከፈተውን ጦርነት ከፌደራል መንግስት ጋር በመቆም በአጭር ግዜ ውስጥ ለማጥራትና የሀገርንና የህዝብን ሰላም ለማረጋገጥ ከመንግስትና ከህዝባዊ መዋቅር ጋር እንሰራለን ብለዋል፡፡

የጥፋት ቡድኑና ተላላኪዎቹ የተስፋ መቁረጥ ጥፋት እንዳይፈፅሙ ህዝቡ ከፀጥታ መዋቅሩ ጋር እንዲሰራ ጥሪ አቅርበዋል፡፡