Fana: At a Speed of Life!

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ፓርቲያቸውን ለመምራት የተደረገውን ምርጫ አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 17፣2012(ኤፍ.ቢ.ሲ) የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የሊኩድ ፓርቲን ለመምራት የተደረገውን ምርጫ አሸነፉ።

ከሊኩድ ፓርቲ  116  ሺህ አባላት መካከል 49 በመቶ ያህሉ ድምጽ የሰጡ ሲሆን፥ ከዚህ ውስጥም ኔታኒያሁ  የ72 ነጥብ 5 በመቶዎቹን ድምፅ በማግኘት አሸንፈዋል።

የኔታኒያሁ ተፎካካሪ 53 ዓመቱ ጌዴዎን ሳአር ሽንፈታቸውን አምነው የተቀበሉ ሲሆን፥ መጋቢት ወር በሚካሄደው አጠቃላይ ምርጫ  ኔታንያሁን እንደሚደግፉ ገልጸዋል።

የ 70 ዓመቱ ጠቅላይ ሚኒስትር በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ለሶስተኛ ጊዜ አጠቃላይ ምርጫ ተካሂዶ መንግስት ለመመስረት የሚያስችል ወንበር ያላገኙበት፣ በጉቦ እና በሙስና ክሶች ችሎት ፊት የቀረቡበት አስቸጋሪ ጊዜን አሳልፈዋል።

ኔታኒያሁ ከድሉ በኋላ ባሰሙት ንግግር በቀጣዩ አጠቃላይ ምርጫ ፓርቲያቸውን ወደ ድል እንደሚወስዱት እና እስራኤልን በመምራት ወደ አልጠተጠበቀ ስኬት እንደሚያደርሷት ተናግረዋል።

ሀገሪቱን ረዘም ላለ ጊዜ በጠቅላይ ሚኒስትርነት ያገለገሉት ኔታንያሁ ባለፈው ወር በሦስት የሙስና ጉዳዮች ላይ ክስ ከተመሰረተባቸው ወዲህ አስቸጋሪ ጊዜን አሳልፈዋል።

ኔታኒያሁ ክሱ መሰረተ ቢስና የፖሊቲካ ሴራ ነው ሲሉ ሲያጣጥሉ ቆይተዋል።

 

ምንጭ፡-ቢ.ቢ.ሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.