የሀገር መከላከያ ሰራዊት የተቃጣበትን ጥቃት በመመከት የህዝቦችን ደህንነትና የሀገሪቱን ሉዓላዊነት በማስጠበቅ ሃላፊነቱን እየተወጣ ነው -ሚኒስቴሩ
አዲስ አበባ ፣ጥቅምት 25 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢፌዴሪ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ በህወሃት የተቃጣበትን ጥቃት በመመከትና በማክሸፍ የሀገሪቱን ሉዓላዊነት በማስጠበቅ ሃላፊነቱን እየተወጣ መሆኑን የመከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ።
ከትናንት ምሽት ጀምሮ በኢፌዴሪ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ የታጠቀ የህወሃት ሃይል ጥቃት በማድረስ ጉዳት ለማስከተል፣ በህዝቦች ደህንነትና በሀገር ሉዓላዊነት ላይ አደጋ በመጋረጥ ሀገሪቱን ለማፍረስ ሙከራ ማድረጉ ሚኒስቴሩ ገልጿል።
ሆኖም መከላከያ ሰራዊቱ የተቃጣበትን ጥቃት በመመከትና በማክሸፍ የህዝቦችን ደህንነትና የአገሪቱን ሉዓላዊነት በማስጠበቅ ሃላፊነቱን እየተወጣ መሆኑን ነው የተገለፀው።
ይህንኑ በአስተማማኝ መልኩ በመፈጸም ስኬታማ ተግባር በዘላቂነት ለማረጋገጥ ከህዝቡ ጋር እየሰራ እንደሆነም ዘገባው አመልክቷል።