Fana: At a Speed of Life!

የእሳትአደጋው ከባድ ጉዳት ከማድረሱ በፊት በቁጥጥር ስር ውሏል-ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)በአዲስ አበባ አዋሬ ገበያ አካባቢ የተነሳው የእሳት አደጋ ከባድ ጉዳት ከማድረሱ በፊት በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታወቁ

በአዲስ አበባ የተከሰተውን የእሳት ቃጠሎ አስመልክተው ምክትል ከንቲባዋ  መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም የእሳትአደጋው ከባድ ጉዳት ከማድረሱ በፊት በቁጥጥር መዋሉን ወይዘሮ አዳነች ጠቁመው÷ የደረሰው የንብረት ውድመት መጠንናየአደጋው መንስኤ በመጣራት ላይ መሆኑን ተናግረዋል።

በዚህምሌሊት ላይ የተከሰተውን የእሳት አደጋ በመቆጣጠር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረጉት የከተማዋ አራሮች፣የኢትዮጵያ አየር መንገድ ፣የኢትዮጵያ አደጋ መከላከል ና በአጠቃላይ በአካባቢው የሚኖሩ ወጣቶችንና የጸጥታ ሀይሉን አመስግነዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.