Fana: At a Speed of Life!

የመከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ክልል ልዩ ሃይልና ሚሊሻ አባላት ስኬታማ ድል አስመዝግበዋል-አቶ ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ ፣ጥቅምት 26 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የመከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ክልል ልዩ ሃይልና ሚሊሻ አባላት ስኬታማ ድል ማስመዝገባቸውን የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አቶ ተመሥገን ጥሩነህ ተናግረዋል፡፡

ርእሰ መሥተዳድሩ በማህበራዊ ገፃቸው ላይ እንደገለጹት ÷እጅግ ስኬታማ ውሎ ነበረን ብለዋል::

የክልላችን ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻ እና የመከላከያ ሰራዊት በየደረጃው ያሉ ዓመራሮች እና አባላት በተቀናጀ መልኩ ያደረጉት ተጋድሎ ስኬታማ ነበርም ነው ያሉት::

በትናንትናው ዕለት በሶሮቃ እና ቅራቅር ከዕኩለ ሌሊት እስከ ረፋድ ተደጋጋሚ ማጥቃት ተሰንዝሮብን ነበር፣ ከረፋድ በኋላ በሰነዘርነው ማጥቃት በርካታ ቦታዎችን ተቆጣጥረናል ብለዋል::

በተቆጣጠርናቸው ቦታዎች ያለው የህዝብ ድጋፍ ድንቅ ነበር፣ በርካታ ያለፍላጎቱ እንዲዋጋ የተገደደ የፀጥታ ኃይል በሰላም እጁን ሰጥቷል ብለዋል፡፡

እዋጋለሁ ብሎ የመረጠም ፊቱን አዙሮ እኛን ሲያግዝ ውሏል ነው ያሉት፡፡

ጦርነት አንፈልግም ስንል ጠላታችን ድህነት ነው ከሚል እንጂ ጦርነት ካለማወቅ አይደለም ያሉት አቶ ተመስገን ዛሬም በሌላ ድል ታጅቦ ያልፋል ብለዋል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.