Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ከመከላከያ ሠራዊት ጎን በመቆም ተገቢውን ድጋፍ ለያደርጉ ይገባል- የፌዴሬሽን ምክር ቤት

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ከመከላከያ ሠራዊት ጎን በመቆም ተገቢውን ድጋፍ እንዲያደርጉ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ጥሪ አቀረበ።

የፌዴሬሽን ምክር ቤት ባወጣው መግለጫ፥ “የሀገራችን ልዩ መለያ የሆነው ጀግናው የሃገር መከላከያ ሠራዊታችን በሰሜኑ የሃገራችን ክፍል ዳር ድንበርንና ሉዓላዊነትን በማስከበር ተልዕኮ ላይ እያለ በደም የሰከሩ፣ ከሃዲና የእናት ጡት ነካሾች አሳቻ ጊዜ ጠብቀው አሳዛኝና አሳፋሪ ጥቃት ፈጽመውበታል” ብሏል።

የመከላከያ ሰራዊት ለረዥም ጊዜያት በትግራይ ሕዝብ ላይ የሚቃጣን ጥቃት ጋሻና መከታ በመሆን ራሳቸውን መስዋዕት በማድረግ ሲከላከሉላቸው መቆየታቸውን ያወሳው ምክር ቤቱ፥ ከዚህም በላይ የተፈጥሮ አደጋ ክስተት ሲከሰት ሲታደጉና በልማት መስኮችም ተሰልፈው በጉልበታቸውና በገንዘባቸው በመርዳት የወገን አለኝነታቸውን ያስመሰከሩ ጀግና የቁርጥ ቀንና የሕዝብ ልጆች ናቸው ሲልም ገልጿል።

ለእነዚህ ለቁርጥ ቀን ጀግኖቻችን ክብር፣ ሽልማትና ሞገስ ሲገባቸው በሚመኩባቸው ወገኖቻችንና ወንድሞቻችን በሚሉት ከሃዲዎች የተፈጸመውን አስነዋሪ ጥቃት ምክር ቤቱ በጽኑ እንደሚያወግዘውም አስታውቋል።

ስለሆነም የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ከአካባቢያቸው ጀምሮ እስከ ሃገር ጠንካራና የተቀናጀ ጥንቃቄ በማድረግ በሚያስፈልገው ሁሉ ከመከላከያ ሠራዊት ጎን እንዲቆሙና ተገቢውን ድጋፍ እንዲያደርጉም የፌዴሬሽን ምክር ቤት ጥሪውን አስተላልፏል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.