የትምህርት ሚኒስቴር ከሀይማኖት አባቶች ጋር እየተወያየ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የትምሀርት ሚኒስቴር በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት የተቋረጠውን መደበኛ ትምህርት በማስቀጠል ሂደት ላይ ከሃይማኖት አባቶች ጋር ውይይት እያካሄደ ይገኛል።
የምክክር መድረኩን የትምህርት ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት በጋራ ያዘጋጁት ሲሆን ÷በመድረኩ ላይ ከፌደራል እና ከክልል የተውጣጡ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ አባላት ተሳትፈዋል፡፡
በዚህም በመማር ማስተማር ሂደቱ ላይ የሀይማኖት አባቶች ሚና ምን መምሰል እንዳለበት ውይይት ተካሄዷል።
በመድረኩ ላይ ኮቪድ 19ን ለመቆጣጠር የወጣውን መመሪያ ለሀይማኖት አባቶች የቀረበ ሲሆን ÷የሀይማኖት አባቶችም በመመሪያው ላይ ውይይት አካሂደዋል።
በመድረኩ የሀይማኖት አባቶቹ መደበኛ ትምህርቱን ለማስቀጠል በሚደረገው ጥረት ውስጥ ትልቅ ሀላፊነት እንዳለባቸው መገለፁን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡