Fana: At a Speed of Life!

ህወሓት የመከላከያ ሰራዊት ላይ የፈጸመው ድርጊት የከሃዲነት እርምጃ ነው – የፌዴራሊስት ኃይሎች ጥምረት

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 26፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ህወሓት የህዝብ ልጅ በሆነው የመከላከያ ሰራዊት ላይ የፈጸመው ድርጊት የከሃዲነት እርምጃና አሳፋሪ ተግባር ነው ሲል የፌዴራሊስት ኃይሎች ጥምረት ገለጸ።
በህወሓት የተፈጸመውን ድርጊትም በጽኑ አውግዞታል።
ህውሓት በሰሜን እዝ በሚገኙ የአገር መካላከያ ሰራዊት ካምፖች ላይ የፈጸመው ድርጊት አንድ ኢትዮጵያዊ ህሊና ካለውና ለህዝብ ቆሜያለሁ ከሚል ቡድንም ሆነ ግለሰብ የማይጠበቅ ነው ብሏል ጥምረቱ ።
“እኔ ካልመራሁ ኢትየጵያ ትፍረስ” በማለት እየሄደበት ያለው መንገድም የተወገዘ መሆኑን የሚያመላክት ድርጊት መፈጸሙን እንዳሳየም ጥምረቱ ገልጿል።
በመሆኑም መንግሥት ለሚወስደው እርምጃ ድጋፍ እንደሚሰጥና የጥምረቱ አባላትም ሆነ ደጋፊዎች ከመንግስት ጎን እንደሚቆሙ በመግለጫው አመልክቷል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.