Fana: At a Speed of Life!

የመከላከያ ሰራዊት ከየትኛውም አቅጣጫ ሊሰነዘር የሚችልን ጥቃት በብቃት መወጣትና መቀልበስ የሚያስችለው ቁመና ላይ ይገኛል – ብልጽግና ፓርቲ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 27 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሀገር ውስጥም ሆነ ከውጭ የሚሰጠውን ማንኛውንም ህዝባዊ ተልዕኮ በብቃት እየፈጸመ ስሙ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ በአፍሪካ ህብረት እና በምስራቅ አፍሪካ በጉልህ የተጻፈለት ጀግናው የመከላከያ ሰራዊት ዛሬም እንደትናንቱ ከየትኛውም አቅጣጫ ሊሰነዘር የሚችልን ጥቃት በብቃት መወጣትና መቀልበስ የሚያስችል ቁመና ላይ እንደሚገኝ የብልጽግና ፓርቲ አስታወቀ፡፡
ፓርቲው ደከመኝን የማያውቀው ሰራዊቱ በማህበራዊና በሰብዓዊ ጉዳዮች ላይ ከህዝብ ጎን ሲሰለፍ መቆየቱን አስታውሷል፡፡
አርሶ አደሩን ከማረስ ጀምሮ ምርቱን ጎተራ እስከማስገባት ባለው ሂደት ውስጥ በማገዝ እንዲሁም ሰዎች በደም እጦት ምክንያት ለሞት እንዳይዳረጉ ደም በመለገስ ማህበራዊ ሃላፊነቱን እንደሚወጣም አንስቷል፡፡
በተጨማሪም የኮሮና ቫይረስ ኢትዮጵያ ከገባበት ጊዜ ጀምሮ ለተቸገሩ፣ አቅመ ደካማ ወገኖች እና ችግር ውስጥ ላሉ የማህበረሰብ ክፍሎች ድጋፍ በማድረግም አለኝታነቱን በተግባር አሳይቷልም ነው ያለው፡፡
በቅርቡ በአጥፊው እና ዘራፊው የህውኃት ቡድን በተቀነባበረው ሀገርን የማጥፋት ሴራ አንዱ አካል የሆነውና ሊተገበር ቀርቶ ሊታሰብ የማይችል ድርጊት በሰሜን ዕዠ መከላከያ ካምፕ ላይ ጥቃት ከመሰንዘሩን በላይ የዘረፋ ሙከራዎች መደረጋቸውንም አውስቷል፡፡
ለህዝብና ለሀገር መሰል ሀገራዊ ተልዕኮዎችን በብቃት መፈጸም ለቻለው ጀግናው የመከላከያ ሰራዊት ምላሹ ጥይት ሆኗልም ብሏል፡፡
ድርጊቱ ህዝብን ያስደነገጠና ሀገርን በገሀድ መካዳቸውን ለኢትዮጵያውያን ያሳዩበት መሆኑን በመጥቀስ፡፡
ለህዝብ ደጀን የሆነን ሰራዊት፣ ከህዝብ ወጥቶ ለህዝብ አለኝታ የሆነ መከላከያ ላይ የተኩስ እሩምታ መከፈቱንም ኮንኗል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.