Fana: At a Speed of Life!

በህወሃት ውስጥ ያለ ቡድን ጀብደኝነት ተወግዶ ኢትዮጵያና ህዝቦቿ የሰላም አየር እንዲተነፍሱ እየተወሰደ ያለውን እርምጃ እንደግፋለን – የኢትዮጵያ ዳያስፖራ የተግባር ምክር ቤት

አዲስ አባበ ፣ ጥቅምት 27 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በህወሓት ውስጥ ያለ ቡድን ጀብደኝነት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከህዝብ ጫንቃ ተወግዶ ኢትዮጵያና ህዝቦቿ የሰላም አየር እንዲተነፍሱ መንግስት እየወሰደ የሚገኘውን እርምጃ እንደግፋለን ሲል የኢትዮጵያ ዳያስፖራ የተግባር ምክር ቤት አስታወቀ።

ምክር ቤቱ ከዋሽንግተን ዲሲና አከባቢው ነዋሪ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ጋራ በመተባበር መግለጫ አውጥቷል።

ኢትዮጵያዊነት ሰላም ወዳድነት ፣ ትእግስት፣ ነጻነት ፣ አብሮነት ብሄራዊ ክብርንና ሀገራዊ ማንነትን የሚጠብቅ፣ የሚያስጠብቅ እና ጥልቅ ማስተዋልና አርቆ አሳብነት ያለው ነው ብሏል መግለጫው።

የዚህን ህዝብ ባህላዊ እሴቶችን ስግብግብነትን መሰረት ያደረገ ወንጀለኛ ሥርዓት ሰፍኖ መቆየቱንም ነው የገለፀው።

በህወሓት ውስጥ ያለ ህገ ወጥ ቡድን በዚህ በተሳሳተ አቅጣጫ የኢትዮጵያን ህዝብ ለ27 አመታት በመምራቱ በሕዝብ ላይ ሥቃይ፣ መከራ፣ ሞት፣ ስደትና እስር በመብዛቱ የኢትዮጵያ ህዝብ መራራ ትግል አድርጎ ህወሓትን ከስልጣን ማስወገድ ቢችልም ላለፉት ሶስት ዓመትት በትግራይ ህዝብ ተሸጉጦ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ጉዳቶችን ሲያደርስ እንደቆየ አስታውቋል።

በመግለጫው ይህ ቡድን እራሱ ያረቀቀውንና ያጸደቀውን ህገ መንግት በመጣስ እንደኖረ ሁሉ አሁንም የተቃወመውን ግለሰብና ማህበረሰብ በማጥፋት በህዝብ ትግል ያጣውን ስልጣኑን መልሶ ለመያዝ መመኘቱን አንስቷል።

ይህንን ስውር ምኞቱንና ሴራውን በፌዴራሊዝም ጽንሰ ሃሳብ ሽፋን ሌሎችን ብሄረሰቦች ለማታለል እንደተጠቀመበት እና በዚህም ያጣውን ስልጣን መልሶ ለመቆጣጠር ሁከት በመፍጠር የአሸባርነት ተግባሩን አስፋፍቷል ብሏል።

በዚህም ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ጉዳቶች ማጋጠማቸውን ያነሳው መግለጫው መንግስት ህገ መንግስቱን ለማስከበር እየወሰደ ያለውን እርምጃ አጠናክሮ እንዲቀጥል ድጋፋቸውን ገልፀዋል።

እንዲሁም መንግስት ህወሓት ሁለተኛ ወደ አጥፊ ተግባሩ እንዳይመለስ ማድረግ እንዳለበትም ገልጿል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.