ም/ከ አዳነች አቤቤ ከአዲስ አበባ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አመራሮች ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 27 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በወቅታዊ የሃገሪቱ ሁኔታ ላይ ከአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አመራሮች ጋር ተወያይተዋል።
ውይይቱን አስመልክተው ምክትል ከንቲባዋ በፌስቡክ ገፃቸው እንዳሉት ÷በህዝብ መካከል ያለውን ፍቅር፣ አብሮነት፣ መቻቻል፣ መደጋገፍ እና መከባበር በማጠናከር ረገድ ያላቸውን ጉልህ ሚና በማዳበር እንደወትሮዉ ከከተማ አስተዳደሩ ጋር ይበልጥ ተረባርቦ መስራት ላይ ለማተኮር መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡