Fana: At a Speed of Life!

በፊሊፒንስ በደረሰው የአውሎ ንፋስ አደጋ የሟቾች ቁጥር 28 ደረሰ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 17፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በፊሊፒንስ በደረሰው አውሎ ነፋስ አደጋ የሟቾች ቁጥር 28 መድረሱ ተሰማ።

የፊሊፒንስ ብሄራዊ የአደጋ ስጋት ቅነሳ እና አመራር ምክር ቤት ማዕከላዊ የሃገሪቱን ክፍል ጨምሮ በ10 የተለያዩ ቦታዎች ሰዎች መሞታቸውን አስታውቋል።

በአደጋው ከሞቱት በተጨማሪም 12 ሰዎች የገቡበት አልታወቀም ነው የተባለው።

አደጋው በ186 ሺህ ሰዎች ላይ ተፅዕኖ ማሳደሩም ነው የተነገረው።

አውሎ ነፋሱ ከ2 ሺህ በላይ ቤቶችና 55 ትምህርት ቤቶች ላይ ጉዳት አድርሷል።

ፊሊፒንስን በተደጋጋሚ በአውሎ ነፋስ መመታቷ ይነገራል።

ምንጭ፡- ሲ ጂ ቲ ኤን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.