Fana: At a Speed of Life!

ለ21 ሺህ የኢንዱስትሪ ፓርክ ሰራተኞች የመኖሪያ ቤቶችን ለማቅረብ እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ለ21 ሺህ የኢንዱስትሪ ፓርክ ሰራተኞች የመኖሪያ ቤቶችን ለማቅረብ እየሰራ መሆኑን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አስታወቀ።

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሳንዶካን ደበበ እና ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚዎች ከዩኤን ሀቢታት የኢትዮጵያ ማናጀር አቶ አክሊሉ ፍቅረስላሴ እና የብሄራዊ ፕሮግራም ኦፊሰር ወይዘሮ ዮሃናን እዮብ ጋር ለኢንዱስትሪ ፓርክ ሰራተኞች የመኖሪያ ቤቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረብ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ግንባታና መስፋፋት ጋር ተያይዞ እየተፈጠሩ የሚገኙ የስራ እድሎችን ተከትሎ በርካታ ሰዎች ከተለያዩ ቦታዎች ፓርኮች ወደ ሚገኙበት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል።

ከመኖሪያ ቤት አቅርቦት ጋር በተያያዘ ከዚህ በፊት የተሰሩ በርካታ ጥናቶችን ከከተማ አስተዳደሮች፣ ከሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ምንጮች ጋር በጋራ በመሰራት ላይ እንደሚገኝ አውስተዋል፡፡

ሁዳዩን በፍጥነት ወደ ተግባር መቀየር እንደሚጠበቅም መግባባት ላይ መደረሱን ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በአሁኑ ወቅት ከ55 ሺህ በላይ ሰራተኞች በፓርኮች ውስጥ በስራ ላይ የሚገኙ ሲሆን፥ ሁሉም ኢንዱስትሪ ፓርኮች ወደ ስራ ሲገቡ ይህ ቁጥር ወደ 250 ሺህ እንደሚያድግ ይጠበቃል።

ኮርፖሬሽኑ የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም ለ21 ሺህ የፓርክ ሰራተኞች የመኖሪያ ቤቶችን ለማቅረብ እየሰራ ነው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.