የሀገር ውስጥ ዜና

በኦሮሚያ ክልል 389 ሺህ ሄክታር መሬት በመስኖ ለማልማት እየተሰራ ነው

By Tibebu Kebede

December 27, 2019

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 17፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኦሮሚያ ክልል 389 ሺህ ሄክታር መሬት በመስኖ በማልማት 200 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ለማግኘት እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ግብርና እና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ አስታወቀ።

የክልሉ ግብርና እና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ሀላፊ አቶ ዳባ ደበሌ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት በመስኖ ልማቱ ስንዴን በስፋት ለማልማት 4 ዞኖች ተለይተዋል።