የሀገር ውስጥ ዜና

ወንጀለኛ አካላት ዕርቅና ድርድር ፈላጊ በመምሰል ከሕግ የበላይነት ሊያመልጡ አይችሉም- ጠ/ሚ ዐቢይ

By Tibebu Kebede

November 07, 2020

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 28፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ወንጀለኛ አካላት ዕርቅ እና ድርድር ፈላጊ በመምሰል ከሕግ የበላይነት ሊያመልጡ እንደማይችሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አስታወቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልእክት ነው ይህንን ያሉት።

በመልእክታቸው አክለውም፥ የሚከናወነው ኦፕሬሽን ዓላማው፣ የሚገባቸውን ቅጣት ሳያገኙ ከገደብ አልፈው የቆዩትን አጥፊ ግለሰቦች እና ቡድኖች በሀገራችን ሕግጋት መሠረት ተጠያቂ ማድረግ ነው ብለዋል።