ኢትዮጵያ ወደ ሕገ መንግሥታዊ ዴሞክራሲ የተሳካ ሽግግር እንድታደርግ የሕግ የበላይነትን መከበር አለበት- ጠ/ሚ ዐቢይ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 28፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያ ወደ ሕገ መንግሥታዊ ዴሞክራሲ የተሳካ ሽግግር እንድታደርግ የሕግ የበላይነትን መከበር እንዳለበት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አስታወቁ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልእክትት፥ የተጀመረውን የዴሞክራሲ ሂደት ከሥርዓት አልበኛ የፖለቲካ ተዋናዮች ለመከላከል አስፈላጊ የሕግ ማስከበር ርምጃዎችን መውሰዱን ይቀጥላል ብለዋል።